1. ቶሎ እርምጃ ወስደን ነገሮች በፍጥነት ባይከናውኑ ኖሮ ይህንን መልአክት አሁን ከቅሊንጦ ሆኜ የምጽፈው ይሆን ነበር፡፡
ዓርብየአዳማ ከሰዓቱሙቀትያየለነበር፤ለሥራነጠልእንድታደርገኝመርጬያትየነበረችውጥግሙቀትሲያይልባትወጣገባማለትጀምሬያሁ፤ቅዳሜማታቴዲአፍሮበሚያዘጋጀውኮንሰርት አንድንገባ አዲስ አበባ እየደዋወልኩ ስጠይቅ ኤዲ (ኤዶም ካሳዬ) እንደማትገኝስትነግረኝትንሽቅርብሎኝነበርቢሆንምቀንቴስት-ኦቭአዲስየምግብፌስቲቫልላይሳልናገርተከስቼየዞን ዘጠኝ ጓደኞቼን እና ሌሎችጓደኞቻችንንሰርፕራይለማድረግዱለታላይነኝ፡፡
የቀኑ መገባደጃ ላይ አንድ አጭር የስልክ መልእክት ወደ ስልኬ ገባ ፡፡ዞላ(ዘላለም ክብረት) ነበር ፡፡ስልክ መልእክቷ እጥርምጥንያለችብትሆንምአንዳንድ ጊዜ የዞን9 አባላት ኦንላየን ያለው የግል ቡድናችን ውስጥ ውይይቶቻችንበድምጽብልጫመወሰንሲኖርብን ወይም ደግሞ የሞቀክርክር እየተደረገ አንድ ሰው ኦፍላየን ሲሆን “ኀረ ወደኢንተርኔት ና እና ሃሳብ ስጥ” አይነት ነገር መልእክት ስልካችን ላይ እንላላካለን፡፡ ከዞላ የመጣውም አጭር መልክት ተመሳሳይነት ነበረው፡፡ ግንይሄኛውበጣምያጠረነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ከዞላ ድጋሚ ሌላ ቴክሰት ተደገመ ፡፡ “they may arrest me” ይላል መልእክቱ ፡፡በድንጋጤወደ ኢንተኔት ስመጣ ሶሊ በሁሉም በኩም መልእክት ስትልክ ደረስኩ ፡፡አብረውየነበሩትአጥኔክስእናየበፍቄስልካቸውአይመልስም፣ማሂከቢሮተወሰደች፣አቤልምእንደዛው፡፡ የሆነ የከፋ ነገር እየተከናወነ ነው ዘግይተው ነው አንጂ እኔ መድረሳቸው እንደማይቀር ተስማማን፡፡

የዚያን ሰሞን ወከባችን ሲበዛና ምን ይሻላል የሚለው ውይይት ሲደጋገም ዞላ ‹‹ምንምበሌለበትኢሕአዴግእኛንካሰረአብዷልማለትነው››ብሎ ይከራከር ነበር፡፡አሁን በአይኔ የማየው የመታሰር ስጋት መልእክት የመጣው ከዞላ ነው፡፡የማህበራዊሚዲያንፈጽሞየማያውቀውደህንነት ናቱን ሲያዋክበው “ናቲ ለደህንነትየትውውቅኮርስ እየሰጠ ነው” ብለን አንቀልድበትም ነበር፡። ናቲን አብረኽን ስራ የሚል ማስፈራራትም ጉትጎታም ሳይቀር ሲያዋክበው ነበር ፡፡ጓደኞቹንአሳፎከሰጠእሱምንምእንደማይሆንሊወተውተውም ሞክሯል፡፡ አሁን የዞላን ንግግር እና እርግጠኝነት ሳስበው በእኛእስኪደርስጠበቅንእንጂካበዱስቆይተውነበር እላለሁ፡፡
የዛው ሰሞን የዞን 9 አባላትየተጠናከረውንየደህንነቶችክትትልተንተርሶከፍተኛእናዝቅተኛየመታሰርእድልያላቸውበሚልከፋፍለን ለማስቀመጥ ሞክረን ነበር፡፡ አገር ቤት ካለነው የመጀመሪያውንደረጃአጥናፍእናበፍቄሲይዙማሂእናእኔ መታሰር ስጋታቸው የመጨረሻውላይነው ብለን ታስበን የነበርነው ነን ፡፡በማሂመያዝ ዜና ይሄንንግምታችንአፈርድሜያበላነበር፡፡ ከዚህ ዜና በኋላ ኦን ላየን ካሉ ጓደኞቼ ነገሩን በማጣራት ፈላጊዎቼእስኪመጡሳልጠብቅ ከስራ ቦታ ላፕቶፔን ብቻ ይዥ ተነስቼ ወጣሁ ፡፡ ስራ ቦታ ሰው ድንገት ከፈለገኝ ለስራ ወደ አዋሳ መሄዴን እና ቶሎ አንደምመለስ ተናግሬ ነበር ፡፡ ወደቤት መሄድ የማይቻል ሃሳብ ሆነ ቀኑም እየተገባደደ በመሆኑ ከስራ ቦታዬ ዞር ያደርገኛል ወዳልኩት አካባቢ ላፕቶፔን ይዥ በፍጥነት አቀናሁ ፡፡ ሥልክማጥፋትእናመቀየር፣በሌላሥምአልጋመከራየት፣እንቅልፍአልባእጅግበጣምረጅም ሌሊትበአምባገነኖችበትርበሃዘንልባችንየተሰበረበትምሽትነበር፡፡ የእኔ ነገር ያንን ምሽት ገና ስላለየለትም የኤዶም ስልክም ዝግ በመሆኑ ግራ እየተጋባንም( እስሩ ለዞን9 ብቻ ነው የመጣው የሚል የዋህ ሃሳብም ነበረን) አንቅልፍ በአይናችን ሳይዞር ነጋ፡፡ ይህ ሌሊት ባለፈ በማግስቱ በእለተ ቅዳሜ አንዲት ነጭ ሸሚዝ እንደለበስኩ ላፕቶፔን ብቻ አንጠልጥዬ የጎረቤት አገር ኤርፓርት ላይ ሶል ተቀበለችኝ ምንም አይነት ኮምንኬሽን ስላልነበረኝ የኤዶምን መታሰር እርግጥ ዜና እና የአስማማውን መታሰርም እዛው ሰማሁ፡፡ ቶሎ እርምጃ ወስደን ነገሮች በፍጥነት ባይከናውኑ ኖሮ ይህንን መልአክት አሁን ከቅሊንጦ ሆኜ የምጽፈው ይሆን ነበር፡፡ (በመትረፌብዙባለማድረጌከእነሱጋርመሆንንብናፍቅም)፡፡